የፌዴራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን በ2014 ግማሽ ዓመት ከ 1 ቢሊዬን በላይ የብር መጠን ያላቸዉ መዝገቦች ላይ ዉሳኔ ሰጠ
********************
የፌደራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን በ2014 ግማሽ ዓመት ለኮሚሽኑ ከቀረቡት የይግባኝ መዝገቦች መካከል 1,422,503,508.00 የብር መጠን የያዙ 307 የይግባኝ መዝገቦች መርምሮ ወሳኔ ሰጠ ፡፡
ኮሚሽኑ በ2013 በጀት ዓመት ዉሳኔ ሳያገኙ ወደ 2014 በጀት ዓመት የዞሩ 299 መዝገቦችን በማካተት በ2014 በጀት ዓመት የጉምሩክ ኮሚሽን 187 የገቢዎች ሚኒስቴር 181 በድምሩ 368 አዲስ የተከፈቱ መዝገቦችን በመያዝ በድምሩ 667 ዉሳኔ የሚሹ የይግባኝ መዝገቦች ለኮሚሽኑ ቀርቦ የታየ ሲሆን ከ667 መዝገቦች መካከል ለ312 የይግባኝ መዝገቦች ዉሳኔ ለምስጠት ተቀጥረዉ ለ307 የይግባኝ መዝገቦች ዉሳኔ መስጠት ተችሏል፡፡
በኮሚሽኑ ዉሳኔ ከተሰጣቸዉ የይግባኝ መዝገቦች መካከል 52 የተሻረ ፣ 15 የተሻሻለ ፣ 187 የፀና ፣ 41 የተዘጋ እና 12 የተመለሱ መዝገቦች ሲሆን በ2014 ግማሽ ዓመት ከ 307 ዉሳኜ ካገኙት መዝገቦች ዉጭ ያሉት 360 መዝገቦች መካከል 47 ለመልስ ፣ 3 ለብይን ፣ 305 ለቃል ክርክር እና 5 ለዉሳኔ የተቀጠረ ሲሆን የኮሚሽኑ የዉሳኔ መስጠት አቅም 98.39% የደረሰ ሲሆን የአፈፃፀም ዉጤት ከ2013 የግማሽ አመት አፈፃፀም ጋር ሲነፃፀር በ2.59% መብለጥ ችሏል፡፡
በተጨማሪም በ2013 የዞሩ እና በ2014 ግማሽ ዓመት ከቀረቡ የይግባኝ መዝገቦች ከገቢዎች ሚኒስቴር 270 የይግባኝ መዝገቦች ሲሆኑ የያዙት የገንዘብ መጠን 1,605,082,317.83 ሲሆን ከጉምሩክ ኮሚሽን የቀረቡ የይግባኝ መዝገቦች ብዛት 397 ሲሆን የያዘዉ የገንዘብ መጠን 838,095,788.97 ነዉ፡፡
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛ አድራሻችንን ይጠቀሙ
ፌስ ቡክ
https://www.facebook.com/taxapco
ቴሌግራም
https://t.me/FTAC2014