Citizen Charter

News

የፌዴራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ለ715 መዝገቦች ውሳኔ ሰጠ፡፡ - Thursday, August 4, 2022

ፌታይኮ

የፌደራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን የኮሚሽኑ ከፍተኛ አመራሮችና ሠራተኞች በተገኙበት በሀርመኒ ሆቴል ሐምሌ 26 ቀን 2014ዓ.ም ለአንድ ቀን ሲያካሂድ በነበረው የተቋሙ ሥራ ግምገማ የ2014 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጻም በመገምገም፣ የ2015 በጀት ዓመት መሪ ዕቅድ ላይ ኦሬንቴሽን በመስጠት ተጠናቋል፡፡

የኮሚሽኑ የፕላንና ለውጥ ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እዮብ አለማየሁ እንደገለጹት፤ ኮሚሽኑ በበጀት ዓመቱ የይግባኝ ቅሬታዎችን በህግና በአሠራር በመመርመር ጥራት ያለው ውሳኔ የመስጠት አቅም (100%) ለማድረስ ታቅዶ ከባለፈው በጀት ዓመት በተለያዩ ምክንያቶች ውሳኔ ሳያገኙ የዞሩ (299) እንዲሁም አዲስ የተከፈቱ (770) በጥቅሉ (1069) የይግባኝ መዛግብት የቀረቡ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ በ (719) መዛግብት ላይ የቃል ክርክር ተደርጎባቸው ለውሳኔ የተቀጠሩ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ (715) መዛግብት ውሳኔ እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡

አክለዉም ውሳኔ ካገኙት መዛግብት መካከል (456) የጉሙሩክ ጉዳዮች ሲሆኑ (259) መዛግብት ደግሞ የገቢዎች ጉዳዮች መሆናቸዉን ገልፀዋል፡፡

የኮሚሽኑ ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ሙልጌታ አያሌው እንደገለጹት፤ ተቋማዊ የአገልግሎት አሠጣጡን በዘመናዊ የቴክኖሎጂ ከማሳደግ አንጻር የኮሚሽኑን የዳታ ቤዝ ሲስተም (Data base system) በማልማት የአገልግሎት አሠጣጡን በኦን ላይን (Online Service) ለመስጠት ታቅዶ የማልማት ሥራው (100%) ተጠናቆ ለተገልጋዩ ምቹ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ አክለዉም የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርትና ቀጣይ እቅድ የኮሚሽኑን ጠንካራ ጎኖች በማጠናከር ክፍትቶችን ለመሙላት ያስችለዋል ብለዋል።

በመጨረሻም የመድረኩ ተሳታፊ ሰራተኞች በቀረበዉ የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶችን አቅርበው ውይይት የተደረገበት ሲሆን በኮሚሽኑ ፕሬዚደንት ቀጣይ አቅጣጫ ተቀምጣል፡፡

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛ አድራሻችንን ይጠቀሙ

ፌስ ቡክ

https://www.facebook.com/taxapco

ድረ ገፅ

https://www.ftac.gov.et

ቴሌግራም

https://t.me/FTAC2014

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛ አድራሻችንን ይጠቀሙ

ፌስ ቡክ

https://www.facebook.com/taxapco

 
የፌዴራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን የ2014 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወር እቅድ አፈፃፀም ገመገመ፡፡ - Friday, April 15, 2022

ሚያዚያ 06 ቀን 2014 ዓ.ም የፌዴራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን የ2014 በጀት ዓመት የዘጠኝ (9) ወር እቅድ አፈፃፀም የኮሚሽኑ ፕሬዚደንት ፣ ዳኞች ፣ አመራሮችና ሰራተኞች በተገኙበት ቦሌ በሚገኘዉ ሳቦን ሆቴል ተገምግሟል፡፡
የመክፈቻ ንግግር በማድረግ ፕግራሙን ያስጀመሩት የኮሚሽኑ ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ሙሉጌታ አያሌዉ  መንግስትና ህዝብ የጣለብንን ሀላፊነት ነፃና ፣ ገለልተኛ በሆነ መልኩ በመስራ ለሌሎች ተቋማት አርዐያ በመሆን የንግዱን ማህበረሰብ የሚያምንብን በህግ እና በመመሪያ ላይ በመመርኮዝ ፈጣን አገልግሎት መስጠት ይኖርብናል ብለዋል፡፡
በመቀጠል ኮሚሽኑ በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወር ጊዜ ዉስጥ በአጠቃላይ የቀረቡ የቅሬታ መዛግብቶች ከገቢዎች 372 ከጉምሩክ 494 በአጠቃላይ 866 ሲሆኑ ከነዚህ ዉስጥ በዘጠኝ ወራት ዉስጥ አዲስ የተከፈቱ ከገቢዎች 193 ከጉምሩክ 336 በአጠቃላይ 567 ሲሆኑ ከነዚህ የቅሬታ መዛግብት ዉስጥ 529ኙ ሲወሰኑ የተቀሩት ለመልስ 40 ፣ ለብይን 3 ፣ ለቃል ክርክር 292 እና ለዉሳኔ 2 በድምሩ 337 መዛግብት ወደ አራተኛ ሩብ ዓመት ተሸጋግረዋል ብለዋል፡፡
አያይዘዉም ጊዜዉ \ቴክኖሎጂ እንደመሆኑ መጠን ኮሚሽኑ አዲስ ባስገነባዉ ዳታ ቤዝ ባለድርሻ አካላቶቿችን ሳይጉላሉ ካሉበት ቦታ በመሆን ጉዳያቸዉን ወይም ቅሬታቸዉን በWWW.ftac.gov.et በመመዝገብ መከታተል እንደሚችሉ ገልፀዋል፡፡
የኮሚሽኑን የ2014 የዘጠኝ (9) ወር የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ያቀረቡት የኮሚሽኑ ፕላንና ለዉጥ ማስተባበሪያ ዳይሬክተር አቶ እዮብ አለማየሁ የዉሳኔ የመስጠት አቅም ለማሳደግ ለዉሳኔ ከተቀጠሩት 531 መዛግብት ዉስጥ ለ529 መዛግብት ዉሳኔ በመስጠት የዉሳኔ የመስጠት አቅማችን 99.6 የደረሰ መሆኑን እና ከባለፈዉ ዓመት ተመሳሳይ ወር ጋር ሲነፃፀር በ5.6 መሻሻል ያሳየ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
በመጨረሻም የመድረኩ ተሳታፊዎች በቀረበዉ የ2014 የዘጠኝ (9) ወር የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶችን አቅርበዉ  ሰፊ ዉይይት የተደረገበት ሲሆን በቀጣይም ምን መሆን እንዳለበት በኮሚሽኑ ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ሙሉጌታ አያሌዉ ቀጣይ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛ አድራሻችንን ይጠቀሙ
ቴሌግራም
https://t.me/FTAC2014
ፌስ ቡክ
https://www.facebook.com/taxapco

 
የፌዴራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት እና አመራሮች የዲጂታል ሀብት ምዝገባ አካሄዱ፡፡ - Tuesday, March 29, 2022

 


የፌዴራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት እና አመራሮች የዲጂታል ሀብት ምዝገባ አካሄዱ፡፡

********************

የፌዴራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን መጋቢት 15 ቀን 2014 ዓ.ም የኮሚሽኑ ፕሬዝዳንት ፣ ዳኞች ፣ አመራሮችና ሰራተኞች በኮሚሽኑ ፅ/ቤት የዲጂታል ሀብት ምዝገባ አካሄዱ፡፡

 

በዲጂታል የሀብት ምዝገባ ስነ-ስርዓቱ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የፌዴራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ሙሉጌታ አያሌዉ የሀብት ምዝገባ ዲጂታል ስርዓት ከወረቀት ነፃ ሆኖ ሀብትን በበየነ መረብ ለማስመዝገብ የሚያስችል የመረጃ ጥራት እና ተደራሽነት የሚጨምር ጊዜ ፣ ወጪ ቆጣቢ ፣ ግልፅነት ፣ ተጠያቂነት ለማስፈን እና የጥቅም ግጭትን ለመከላከል የሚረዳ ነዉ በማለት የዲጂታል ሀብት ምዝገባዉን በቀዳሚነት በመመዝገብ አስጀምረዋል፡፡

 

አያይዘዉም ሁሉም የኮሚሽኑ ዳኞች አመራሮች እና ሰራተኞች ዲጂታል የሀብት ምዝገባ የአሰራር ስርዓት የሚጠይቀዉን በሙሉ በቅንነትና በታማኝነት መመዝገብ እና ሌሎችም እንዲያስመዘግቡ ማበረታታት እና  ሀገራዊ ግዴታቸዉን እንዲወጡ አበክረዉ ተናግረዋል፡፡

 

የፌዴራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ዳይክቶሬት ጀማሪ ባለሙያ የሆኑት ወ/ሪት ትዕግስት ጥላዬ ስለ ዲጂታል የሀብት ምዝገባ የአሰራር ስርዓት ለኮሚሽኑ ዳኞች ፣ አመራሮች እና  ሰራተኞች ኦሬቴሽን ሰተዋል፡፡

 

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛ አድራሻችንን ይጠቀሙ

ፌስ ቡክ

https://www.facebook.com/taxapco

ቴሌግራም

https://t.me/FTAC2014

 
የፌዴራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን በ2014 ግማሽ ዓመት ከ 1 ቢሊዬን በላይ የብር መጠን ያላቸዉ መዝገቦች ላይ ዉሳኔ ሰጠ - Tuesday, March 29, 2022

የፌዴራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን በ2014 ግማሽ ዓመት ከ 1 ቢሊዬን በላይ የብር መጠን ያላቸዉ መዝገቦች ላይ ዉሳኔ ሰጠ

********************

የፌደራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን በ2014 ግማሽ ዓመት ለኮሚሽኑ ከቀረቡት የይግባኝ መዝገቦች መካከል 1,422,503,508.00 የብር መጠን የያዙ 307 የይግባኝ መዝገቦች መርምሮ ወሳኔ ሰጠ ፡፡

 

ኮሚሽኑ በ2013 በጀት ዓመት ዉሳኔ ሳያገኙ ወደ 2014 በጀት ዓመት የዞሩ 299 መዝገቦችን በማካተት በ2014 በጀት ዓመት የጉምሩክ ኮሚሽን 187 የገቢዎች ሚኒስቴር 181 በድምሩ 368 አዲስ የተከፈቱ መዝገቦችን በመያዝ በድምሩ 667 ዉሳኔ የሚሹ የይግባኝ መዝገቦች ለኮሚሽኑ ቀርቦ የታየ ሲሆን ከ667 መዝገቦች መካከል ለ312 የይግባኝ መዝገቦች ዉሳኔ ለምስጠት ተቀጥረዉ ለ307 የይግባኝ መዝገቦች ዉሳኔ መስጠት ተችሏል፡፡

 

በኮሚሽኑ ዉሳኔ ከተሰጣቸዉ የይግባኝ መዝገቦች መካከል 52 የተሻረ ፣ 15 የተሻሻለ ፣ 187 የፀና ፣ 41 የተዘጋ እና 12 የተመለሱ መዝገቦች ሲሆን በ2014 ግማሽ ዓመት ከ 307 ዉሳኜ ካገኙት መዝገቦች ዉጭ ያሉት 360 መዝገቦች መካከል 47 ለመልስ ፣ 3 ለብይን ፣ 305 ለቃል ክርክር እና 5 ለዉሳኔ የተቀጠረ ሲሆን የኮሚሽኑ የዉሳኔ መስጠት አቅም 98.39% የደረሰ ሲሆን የአፈፃፀም ዉጤት ከ2013 የግማሽ አመት አፈፃፀም ጋር ሲነፃፀር በ2.59% መብለጥ ችሏል፡፡

 

በተጨማሪም በ2013 የዞሩ እና በ2014 ግማሽ ዓመት ከቀረቡ የይግባኝ መዝገቦች ከገቢዎች ሚኒስቴር 270 የይግባኝ መዝገቦች ሲሆኑ የያዙት የገንዘብ መጠን 1,605,082,317.83 ሲሆን ከጉምሩክ ኮሚሽን የቀረቡ የይግባኝ መዝገቦች ብዛት 397 ሲሆን የያዘዉ የገንዘብ መጠን 838,095,788.97 ነዉ፡፡

 

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛ አድራሻችንን ይጠቀሙ

ፌስ ቡክ

https://www.facebook.com/taxapco

ቴሌግራም

https://t.me/FTAC2014

 
የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ እና ተጠሪ ተቋማቱ የአቅመ ደካሞችን ቤት ግንባታ የማከናዉን ሥራ አስጀመሩ - Thursday, September 2, 2021

 

የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ እና ተጠሪ ተቋማቱ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ለሚኖሩ የ15 አቅመ ደካሞች ቤት ግንባታ የማስጀመሪያ መርሐ ግብር አከናወኑ፡፡

ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ እና ተጠሪ ተቋማቱ በመንግስት የተሰጣቸውን ኃላፊነት በተጨማሪ በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ መሳተፍ ወሳኝ መሆኑን በማመን በጋራና በተቀናጀ መልኩ ይህ በጎ ተግባር መጀመሩን በዕለቱ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ምክትል ሥራ አሰፈጻሚ ለዚህም ምስጋና አቅርባል፡፡

ሰለሆነም በዛሬው ዕለት ከሚካሄደው የቤት ግንባታ በተጨማሪ የቤት ቁሳቁሶች እንደሚያሟሉም የፕሮግራሙ አሰተባበሪ አቶ ገብሩ ገልጻል፡፡

በዚህ የክረምት መርሐ ግብር የ24 የአቅመ ደካሞች ቤት ለማደስ የታቀደ ሲሆን የ15ቱ ቤቶች ግንባታ በዛሬው ዕለት የተጀመረ ሲሆን ቀሪዎቹ ደግሞ ግንባታቸው በጥቂት ቀናት ውስጥ እንደሚጀመር ተገልጿል።

ግንባታውን ያስጀመሩት የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ በየአመቱ የምናደርገው የቤት እድሳት የተለያዩ መስሪያ ቤቶችን እና ባለሀብቶችን በማሳተፍ ባህል ልናደርገው ይገባል ብለዋል።

በዚህ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የፌደራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ ሙሉጌታ አያሌዉ የሚታደሱ ቤቶችን በማፍረስ የማስጀመር ሥራ እና የችግኝ ተከላ አከናዉኗል፡፡

ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ እና ተጠሪ ተቋማቱ ከአዲስ አበባ ውጪ በሞጣ ከተማ አዲስ ከተማ በተባለ ስፍራም የ8 አቅመ ደካሞች ቤት እያሳደሰ መሆኑ ይታወሳል፡፡

 
ለኮሚሽኑ የሚቀርቡ መዛግብቶች አዲስ ወዳስገነባዉ ሲስተም ላይ ማስገባት ተጀመረ፡፡ - Thursday, September 2, 2021

 

የፌዴራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን የኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ ሀላፊ የሆኑት አቶ ዮናስ ቀለሙ እንደገለፁት ቅሬታ የቀረበባቸዉን መዝገቦች ስኳን መደረጋቸዉ እና ወደ አዲሱ ሲስተም መግባታቸዉ ያለዉ ጠቀሜታ የይግባኝ ባዮች ሰነዶች እና ፋይሎች ሳይበላሹ ለረጅም ጊዜ እንዲቆዩና በተፈለገዉ ጊዜ እና ሰዓት የምንፈልጋቸዉን መዛግብቶች በፍጥነት ማግኘት እንድንችል ከማገዙም በተጨማሪ በኮሚሽኑ ያሉ መዝገቦች በቋሚነት ሳይበላሹ backup ለመያዝ እና በአጠቃላይ ከማንዋል አሰራር በመዉጣት ስራዎችን ጊዜዉ በፈቀደዉ ሲስተም መጠቀሙ አስፈላጊ መሆኑን አሳዉቋል፡፡

የፌዴራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን የሚሠጣቸውን አገልግሎቶች ለማዘመን እና የተገልጋዮቹን ማመልከቻ በጥራት ለመመልከት ያስችለው ዘንድ አዲስ የኦንላየን የታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ዳታ ቤዝ ሲስተም አስገንብቶ በቅርቡ ወደ ሥራ መግባቱ ይታወቃል፡፡ ይህ የኦንላየን የታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ዳታ ቤዝ ሲስተም የታክስ ወይም የቀረጥ ይግባኝ አቅራቢዎች ጉዳያቸውን በኦንላየን ማመልከቻ በመሙላት እና አስፈላጊ እና ተያያዥ ሠነዶችን በማያያዝ ማመልከቻቸውን ካሉበት ሆነው እንዲያስገቡ እና እንዲከታተሉ የሚያስችል ስርዓት ሲሆን ኮሚሽኑም ከዚህ በፊት የነበሩትን መዛግብቶችን እስካን በማድረግ ወደ መረጃ ቋት (storage server) በማስገባት ላይ ይገኛል፡፡

በቀጣይም ተገልጋዮች የሚጠቀሙበት ዌብ ሳይት WWW.ftac.gov.et መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡

 
የኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የፌደራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ጎበኙ ፡፡ - Thursday, September 2, 2021

 

ክቡር ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ በግብኙታቸው ወቅት ኮሚሽኑ በተለይም ከባለድርሻ አካላት ከገቢዎች ሚኒስቴር ፣ ከጉምሩክ ኮሚሽን ጋር ያለዉን የሥራ ግንኙት የተጠናከረ መሆን እንዳለበት ጠቁሞ በተቋሙ ውሰጥ እየተሰጠ ያለው ገለልተኛ የሆነ የዳኝነት ሥርዓት፣ አገልግሎትን ለተገልጋዩ ቅርብ ለማድረግ የተጀመረው የኦንላይ (E-service) አገልግሎት፣ መዛግቢቶችን ዲጂታላይዝ ለማድረግ የተጀመረው ሥራ እና አጠቃላይ ምቹ የሥራ ቦታን ለመፈጠር የተከናወኑ ተግባራት የሚበረታታ በመሆኑ በዚሁ መቀጠል እንዳለበት ያላቸውን አድናቆት ገልጻል፡፡

የኮሚሽኑ ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ ሙሉጌታ አያሌዉ እና የፕላንና ለውጥ ማሰተባበሪያ ዳይሬክተር አቶ እዩብ አለማየሁ ተቋሙ ሥራ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በመንግስት የጣለበትን ኃላፊነት ለመውጣት የተከናወኑ ዋና ዋና እና ውጤት የተገኘባቸውን ተግባራት ላይ ዝርዝር ማብራሪያ ለክቡር ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ ሰጥተዋል፡፡

 
የፌደራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ሲያካሂድ የነበረውን የግምገማ መድረክ አጠናቀቀ *********************************************** - Thursday, September 2, 2021

 

የፌደራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን የኮሚሽኑ ከፍተኛ አመራሮችና ሠራተኞች በተገኙበት ከነሐሴ 17-18 ቀን 2013 ዓ.ም ለሁለት ቀናት ሲያካሂድ በነበረው የተቋሙ ሥራ ግምገማ የ2013 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጻም በመገምገም፣ የ2014 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ኦሬንቴሽን በመስጠት እና የተገልጋዮች እርካታ ላይ የተጠናውን ጥናታዊ ጽሁፍ ቀርቦ ወይይት በማድረግ ተጠናቋል፡፡

ኮሚሽኑ በ2013 በጀት ዓመት ውስጥ በርካታ ተግባራትን ያከናወነ ሲሆን በተለይም በበጀት ዓመቱ በይግባኝ ከቀረቡ 771 መዝገቦች ውስጥ 765ቱ ውሳኔ ማግኘት ተችላል፡፡ በዚህም ከገቢዎች ሚኒስቴርና ጉምሩክ ኮሚሽን ከ3.3 ቢሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ መዝገቦች መታየቱን ተገልጻል፡፡

ኮሚሽኑ በግብር ሰብሳቢዉ የሚጣሉ የታክስ ቅሬታዎችን የሚያይ በመሆኑ ከቀረቡት ውስጥ 147 መዝገቦች ውሳኔያቸው ተሽሮ ለተገልጋዮች ውሳኔ ተሰጥቷል፡፡ በዚህም የኮሚሽኑ ገለልተኝነት በህብረተሰቡ ላይ አመኔታ እየጨመረ መምጣቱን ያመላክታል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ከባለድርሻ አካላት ጋር ያለዉ የተቀናጀ የሥራ ግንኙነት መኖሩን፣ ተገልጋዮች እንዳይቸገሩ የኮሚሽኑን አገልግሎት ካሉበት ቦታ ሆነዉ ማንኛዉም ቅሬታዎችን በኦንላይን መመዝገብ የሚያስችል ዳታ ቤዝ ተዘጋጅቶ አገልግሎት መጀመሩን የኮሚሽኑ ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ ሙሉጌታ አያሌው ገልጸዋል፡፡

በማጠቃለልም የ2014 በጀት ዓመት ዕቅድ ቀርቦ ውይይት ከተደረገበት በኃላ የዘርፉ አመራሮች ከኮሚሽኑ ፕሬዚዳንት ጋር የዕቅድ ውል ስምምነት እንዲፈራረሙ ተደርጓል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በ2013 በጀት ዓመት በአላማ አሰፈጻሚ ዘርፍ የላቀ አፈጻጸም ላላቸው ሠራተኞች ሽልማት ተበርክቶላችዋል፡፡

 

 

 

 
የኮሚሽኑ መደበኛ ችሎት ለአንድ ወር ዝግ ሆኖ ይቆያል - Thursday, September 2, 2021

የፌዴራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ነፃና ገለልተኛ በሆነ መልኩ የይግባኝ አቤቱታዎችን ተቀብሎ በማከራከር ዉሳኔ እንደሚሰጥ የሚታወቅ ሲሆን ከነሀሴ 1/2013ዓ.ም እስከ መስከረም 9/2014ዓ.ም ድረስ ለአንድ ወር ዝግ የሚሆን ሲሆን መደበኛ ችሎት ዝግ ቢሆንም የኮሚሽኑ ዳኞች የይግባኝ አቤቱታዎችን በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡

በሌላ በኩል ወደ ኮሚሽኑ አገልግሎት ፈልጎ የሚመጣ ባለጉዳይ ከችሎት ዉጭ ሁሉንም አገልግሎት ማግኘት የሚችል ሲሆን ከነዚህም ዉስጥ የንግዱ ማህበረሰብ ይግባኝ ማቅረብ ፤ ዉሳኔ መዉሰድ ፣ የመልስ መልስ ማቅረብ ፣ አስተያየት ማቅረብ ፣ የፍ/ቤቶችን ትዕዛዝ እና አቤቱታ ማቅረብ ተጠቃሾች ናቸዉ፡፡

በመጨረሻም የኮሚሽኑ መደበኛ ችሎት ከመስከረም 10/2014ዓ.ም ጀምሮ አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑን ከወዲሁ ለመግለፅ እንወዳለን፡፡

 
የፌደራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን አመራሮችና ሰራተኞች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ለመስጠት ቃል ገቡ - Thursday, September 2, 2021

“ ኢትዮጵያን ለማዳን እዘምታለሁ ! የትም ፣ መቼም በምንም ” በሚል መሪ ቃል በሀገር አቀፍ ደረጃ ህብረተሰቡ ለመከላከያ ሠራዊት ያለውን ክብር እየገለፀ እንደሚገኝ ይታወቃል ።

ይህን ሀገራዊ ጥሪ በመቀበል የኮሚሽኑ አመራሮችና ሰራተኞች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ የሚያደርጉበትን ሁኔታ ለማመቻቸት የሚያስችል በርካታ ሥራዎችን ማካናወን ላይ ይገኛሉ፡፡

በዚሁ መሰረትም አመራሮቹና ሰራተኞቹ ከወር ደሞዛቸው ላይ ድጋፍ ለመስጠት ቃል የተገባዉን ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ለሚመለከተው አካል ማሰረከብ ተችላል፡፡ በሌላ በኩል የደም ልገሳ እና የቁሳቁስ ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብተዋል፡፡

ከዚህ ተጨማሪም አገራዊ ሰላምን ለማስፈን በሚደረገው ጥረት ከሰራዊቱ ጎን በንቃት እንደሚሳተፉም ገልፀዋል፡፡

 
የፌዴራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ውጤታማ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑ ተገለጸ - Wednesday, September 2, 2020

የፌዴራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን አመራሮችና ሰራተኞች በዳታ ቤዝ ሲስተም ዙሪያ ስልጠና እየወሰዱ ነዉ፡፡------------------------------------------------

የፌዴራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ዳታ ቤዝ ሲስተም ወደ ትግበራ ሊገባ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይህንንም ተከትሎ የኮሚሽኑ አመራሮችና ሰራተኞች በሶስት ዙር በዳታ ቤዝ ሲስተም ዙሪያ ስልጠና  እየወሰዱ ይገኛል ፡፡

 

የፌዴራል ታክስ ይግባኝ የኮምሽን ፕሬዝዳንት አቶ ሙሉጌታ አያሌው ኮሚሽኑ በአዲስ መልክ በአዋጅ ቁጥር 983 /2008 ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ በርካታ ውጤታማ ስራዎችን ማከናወኑን ገልጸዋል፡፡

የፌዴራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን፣ ውጤታማ፣ ፈጣን ተደራሽ ግልፅነትና ተጠያቂነት ያለው ተቋም መገንባትን ራዕይ በማንገብ የታክስከ ፋዩን ማህበረሰብ ቅሬታ በተደራጀና በተፋጠነ መልኩ መፍታት አላማው አድርጎ መቋቋሙን አስታውሰው ለተግባራዊነቱ ርብርብ እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡

እንደ አቶ ሙሉጌታ ገለጻ፣ ኮሚሸኑ በታክስ ሕጎች አተረጓጎም ረገድ በታክስ አስተዳደሩ ውስጥ በሚፈጠረው ልዩነት ምክንያት ታክስ ከፋዩ ሲያጋጥመው የነበረውን እንግልት ለማስቀረት የሚያስችል ወጥነት ያለው የአተረጓጎም ስርዓት እንዲኖር ከማድረጉም በተጨማሪ ታክስ ከፋዮች የሚኖራቸውን ቅሬታ ማቅረብ የሚችሉበት ስርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ በአዲስ መልክ እንዲደራጅ ተደርጓል፡፡

በአዲስ መልክ ስራውን ከጀመረ 8 ወራትን ያስቀጠረው ተቋሙ ቀደም ሲል በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ጽ/ቤት ተብሎ ይጠራ እንደ ነበር ያስታወሱት የኮሚሽኑ ፕሬዝዳንት፣ መንግስት ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት በመስጠት እና የህብረተሰቡን ችግሮች በተቀላጠፈ መንገድ ለመፍታት እንዲያስችል ራሱን ችሎ በኮሚሽን ደረጃ መቋቋሙን ገልጸዋል፡፡

ስራው ቀደም ሲል ከጠቅላይ አቃቤ ህግ፣ ከንግዱ ማህበረሰብ፣ ከገቢዎችና ሌሎች ጋር በጋራ በመሆን በኮሚቴ መልክ የሚሰራ ስራ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በርካታ ችግሮች የነበሩ በመሆኑ ይህንን ለመቅረፍ በሞያቸው ገለልተኛ የሆኑ ዳኞች እንዲሾሙ ተደርጓል ብለዋል አቶ ሙሉጌታ በንግግራቸው፡፡
ኮሚሽኑ በአዲስ መልክ ከተደራጀ በኋላ የተቋሙን መዋቅር የመስራትና የማፀደቅ፣ ራዕይ ፣ ተልዕኮና እሴቶችን የመቅረፅ፣ የተቋሙን መሪ እቅድ፣ እንዲሁም ለተቋሙ ስራ የሚረዱ መመያዎችንና ደንብቦችን በማውጣት ረገድ የታክስ ከፍዩን ማህበረሰብ እንግልት በሚቀንስ መልኩ በመስራት ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

ተቋሙ 930 መዝገቦችን የመረመረ ሲሆን 423 መዝገቦች ተሰርተው የተጠናቀቁ ፣ 359 መዝገቦች ለክርክር በሂደት ላይ ያሉ እና 148 መዝገቦች ደግሞ በቀጣይ አጭር ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አቶ ሙሉጌታ ተናግረዋል፡፡

ተቋሙ ከባለድርሻ አካላት ጋር ያለውን ግንኙነት ለማዳበር፣ የህግ ክፍተቶችን ለመለየት እና ችግሮች ላይ ለመምከር በቀጣይ የተለያዩ መድረኮችን እንደሚያዘጁም የኮሚሽኑ ፕሬዝዳንት ጠቁመዋል፡፡

በመጨረሻም፣ መንግስት የግብር ከፋዩን ማህበረሰብ ቅሬታ ለመፍታት ገለልተኛ የሆነውን የታክስ ይግባኝ ኮሚሽን የተቋቋመ በመሆኑ፣ ማንኛውም በሚከፍለው ታክስ ቅር የተሰኘ አካል አቤቱታውን ለታክስ ይግባኝ ኮሚሽን በማቅረብ የታክስ አስተዳደሩ ይበልጥ ቀልጣፋ፣ ውጤታማና ተገማች እንዲሆን የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት አቶ ሙሉጌታ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

 

 
የፌዴራል ታክስ ይግበኝ ኮሚሽን ከንገዱ ማኅበረሰብ ጋር እንደሚሰራ ገለፀ - Wednesday, September 2, 2020

የፌዴራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ከኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት፣ ከአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፣ ከተለያዩ አስመጪና ላኪ ማህበራት እና አምራች ማህበራት እንዲሁም ከተለዩ የንግዱ ማህበረሰብ ተወካዮች ጋር በኮሚሽኑ አሰራር ላይ ጥቅምት 13 ቀን 2012 ዓ.ም በቦሌ አንባሳደር ሆቴል መሰብሰቢያ አዳራሽ ውይይት አድርጓል፡፡

የኮሚሽኑ ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ ሙሉጌታ አያሌው በውይይት መድረኩ እንደገለፁት ተቋሙ በ2011 ዓ.ም በአዲስ መልክ በኮሚሽን ደረጃ የተቋቋመና እየተደረጀ የሚገኝ ተቋም ሲሆን የኮሚሽኑ ተግባርና ኃላፊነት፣ መመሪያና አሰራር እንዲሁም በስራ ላይ ስለሚያጋጥሙ ተግዳሮቶች ዙሪያ ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር ለመወያየት መድረኩ መዘጋጀቱን ጠቁመዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ አክለውም ኮሚሽኑ በገለልተኛነት ጉዳዮችን በፍታብሄር ህግ፣ በታክስ አስተዳደር አዋጅ፣ በጉሙሩክ አዋጅና የኮሚሽኑ መመሪያ ማዕከል በማድረግ ስራዎችን በማከናወን ላይ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ተቋሙ በቀጠይም ፍትሃዊ ውሳኔዎችን ለተገልጋዮቻችን በመስጠት የታክስ ከፋዩ ማህበረሰብ ግብርን በግልፅነት እንዲከፍል የበኩሉን አስተዋፅኦ እንደሚያበረክት በመድረኩ ተገልጿል፡፡

ከንግዱ ማህበረሰብ የመጡ ተሳታፊዎችም በበኩላቸው ተቋሙ በአዲስ መልክ መደራጀቱን አድንቀው በአገሪቱ የታክስ አስተዳደር ዙሪያ በርካታ ችግሮችን መኖራቸውን በማንሳት ይህ ተቋም በገለልተኝነት ፍትሃዊ ውሳኔዎችን እንዲሰጥ በቂ የሂሳብ እውቀት ያላቸው ባለሞያዎች ሊያማክር ወይም ሊቀጥር ይገባዋል በማለት አስተያዬታቸውን ሰጥተዋል፡፡